የኢትዮጵያ
ምግብ
የኢትዮጵያ ባህላዊና ዘመናዊ ምግብ በስዊስ አገር (ስዊዝርላንድ) እናቀርባለን
ጣዕመ ኢትዮጵያ
የኢትዮጵያ
ምግብ
የኢትዮጵያ ባህላዊና ዘመናዊ ምግብ በስዊስ አገር (ስዊዝርላንድ) እናቀርባለን
ታሪካችንን ያንብቡ
ከሁለት ዓመታት በፊት “ጋስትሮ” ምግብና መጠጥ ቤት «The Alehouse-Palmhof» ከፈትን፡፡
እንግዲህ ወደ ኋላ መለስ ብለን ያዳበርነውን ልምድ መመልከት ይቻላል፡፡ የጀመርነው ሥራ ባልደራብዬ (ሽርካዬ) የሆነው ዮናታን ኃይሌ ጃኮብሰንና እኔም ያሬድ ኃይለ ሥላሴ ከተለያዩ ክፍላተ ዓለማት ጥራታቸው ከፍ ያሉ ከ100 በላይ የተለያዩ ቢራዎችን አስመጥተን በማከፋፈል ላይ ተሰማራን፤ አሁን ልዩ ልዩ የወይንና የማር ጠጆች እንዲሁም በዘመናዊ ፋብሪካ የተመረተ ካቲካላም (ብልጧ!) ካሉን ምርቶች ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ከ25.7. እስከ 11.8.2019 እ.አ.አ. ድረስ በዋናው የምግብ ቤታችን «The Alehouse-Palmhof» አሳምረንና ጥራቱን አስጠብቀን ልዩ ልዩ የባሕል ምግብና መጠጦች አቀርበናል፡፡ እጅ ከሚያስቆረጥሙ የጾምና እስከ ዝነኛው ምርጥ የጉራጌ ክትፎ በኢትዮጵያ ባለሙያዎች አዘጋጅተን ነበር፡፡
በስዊስ ጥራትና ጽዳት ለእንግዶቻችን የተለመዱ መጠጦች ከቤቱ ምግቦች ጋር ጎን ለጎን ይቀርባሉ፤ ከዚህም በተጨማሪ የንግድ ምልክታችን የሆነው ከ20 ያላነሱ የተለያዩ ድራፍት ቢራዎች ቅዝቅዝ ብለው ይጠባበቃሉ፡፡ ሰፊው በረንዳችን ለበጋው አየር ዘና ለማለት ምቹና ዝግጁ ነው፡፡
The Alehouse-Palmhof, Universitätstrasse 23, 8006 Zürich ይሁን፣ ሥልክ +4144 542 87 45